ጀርመን በሩሲያ ነዳጅ ዘይት ላይ የተጣለውን ማዕቀብ እንድትቀበል የአውሮፓ ፓርላማ አባላት አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመን በሩሲያ ነዳጅ ዘይት ላይ የተጣለውን ማእቀብ ማክበር ይኖርባታል ሲሉ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት አሳሰቡ፡፡
በአውሮፓ ፓርላማ ከሁሉም የፖለቲካ ቡድኖች የተውጣጡ ሕግ አውጪዎች ቡድን ጀርመን በሩሲያ የኃይል ምንጮች ላይ እገዳ እንድትጥል ማሳሰባቸው የተሰማው የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ 6ኛውን ማእቀብ በዚህ ሳምንት መገባደጃ አካባቢ ሊጥል ይችላል ሚሉ መረጃዎች እየወጡ ባሉበት ወቅት መሆኑን ዘገባው አንስቷል፡፡
50 የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የጀርመኑ መራኂ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ የኃይል ምርት አስመጪዎች ላይ ከባድ ማዕቀብ ለመጣል የምታደርገውን ጥረት በሃላፊነት እንዲመሩ መጠየቃቸውም ተመለክቷል፡፡
የጀርመን መንግስት በታሪክ ተወቃሽ የሚያደርገውን ስራ እንደማይሰራ እናምናለን ሲሉም የፓርላማ አባላቱ መግለጻቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡