Fana: At a Speed of Life!

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በህዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እቅድ አውጥተው እየሰሩ መሆኑን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅዶችን አውጥተው እየሰሩ መሆኑን የደቡብ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች አስታወቁ።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ከህዝቦች ለተነሱ ጥያቄዎች እንደ አንገብጋቢነታቸው እና ነባራዊ ሁኔታ ችግሮቹን በመለየት በአጭር ፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ እቅድ ለመፍታት እየሰራን ነው ብለዋል።

አቶ እርስቱ ይርዳው የክልሉ ህዝቦች በውይይቶቹ አብዛኛውን ተመሳሳይነት ያላቸው ጥያቄዎች እንዳነሱ ጠቅሰው በተለይ ግን የመሰረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር ፣የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊ እና የሰላምና ፀጥታ፣ የህግ የበላይነት እና የስራ እድል ፈጠራ በቀዳሚነት የተነሱ ችግሮች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው÷ በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማት ፣ የድልድይ ግንባታ፣ የኑሮ ውድነትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ሰላምና ፀጥታ በቀዳሚነት በክልሉ ነዋሪዎች አስቸኳይ እልባት እንዲሰጥ የተነሱ ነጥቦች መሆናቸውን አመላክተዋል።

አመራሮቹ ችግሮቹን በመለየት በአጭር ፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ እቅድ ለመፍታት እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ ቅድሚያ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ እንዲሁም የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ትኩረት እንደሚሰጠው ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የኑሮ ውድነቱን ለመከላከል ከጓሮ እስከ ማሳ የዘለቀ የተቀናጀ የተግባር ስራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የተጀመሩ መሰረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት መስራትና በክልል አቅም ማለቅ የሚገባቸው የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን ፈጥኖ ማጠናቀቅ ላይ እየሰሩ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በሙሀመድ አሊ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.