የሀገር ውስጥ ዜና

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በህዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እቅድ አውጥተው እየሰሩ መሆኑን አስታወቁ

By Feven Bishaw

April 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅዶችን አውጥተው እየሰሩ መሆኑን የደቡብ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች አስታወቁ።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ከህዝቦች ለተነሱ ጥያቄዎች እንደ አንገብጋቢነታቸው እና ነባራዊ ሁኔታ ችግሮቹን በመለየት በአጭር ፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ እቅድ ለመፍታት እየሰራን ነው ብለዋል።

 

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!