Fana: At a Speed of Life!

አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን በአግባቡ መጠቀም የጠነከረች ኢትዮጵያን የመገንባት እድል ነው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን በአግባቡ መጠቀም ከቻልን ከምንጊዜም በላይ የጠነከረች ኢትዮጵያን የምንገነባበት እድል ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር አንዳርጋቸው ተስፋሁን÷ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን ማቋቋም ብቻ ሳይሆን ዋናው ስራው ነው ውጤት የሚያመጣው ይላሉ።

በምክክር ኮሚሽኑ ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ መስራትም ለሚፈለገው ውጤት ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ሂደቱ ከጅምሩ ጥሩ ከሆነ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት አዳጋች እንደማይሆንም ነው የተናገሩት፡፡

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ አቶ ሱራፌል ጌታሁን በበኩላቸው ÷ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎችን በመጥቀስ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አንዱ የስልጣኔ መገለጫ መሆኑን አንስተዋል።

የአገራዊ የምክክር መድረኩ የኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚፈቱበት እና ትልቅ ውጤት የሚመጣበት እንደሚሆን የሂደቶቹ ጅማሬዎች እንደሚያሳዩም ገልፀዋል።

ምሁራኑ ኮሚሽኑ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ህብረተሰቡ መደገፍ እና ከኮሚሽኑ ጎን መቆም ይጠበቅበታል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

በዙፋን ካሳሁን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.