የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በግብርናው የንግድ ዘርፍ ሴቶችን ማሳተፍ እንደሚገባ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምግብ እራስን ለመቻል እና የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በግብርናው የንግድ ዘርፍ ሴቶችን ማሳተፍ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡
ሴቶች በግብርናው ንግድ ላይ ለሚኖራቸው ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት መፍትሄ ማመላከት ያለመ እና “የሴቶችን ተሳትፎ በአግሪ ቢዝነስ እናጎልብት” በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ የአበባ አምራችና ላኪወች ማኅበር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ ዐውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በዚሁ ወቅት የውይይቱ ተሳታፊዎች÷ “በምግብ እራስን ለመቻል እና የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በግብርናው የንግድ ዘርፍ ሴቶችን ማሳተፍ እና ማበረታታት ይገባል” ብለዋል፡፡
ሴቶች በግብርናው ዘርፍ ላላቸው ተሳትፎ እውቅና አለመስጠት፣ የፋይናንስ እጥረት፣ የሰላም እጦት፣ ለሴቶች የሚሰጠው ግምት ማነስ እና የመሳሰሉት ተግዳሮቶች÷ ሴቶች በግብርናው የንግድ ዘርፍ እንዳይሳተፉ እና ውጤታማ እንዳይሆኑ ተግዳሮት መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡
በቅድስት አባተ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!