Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አጎራባች አካባቢዎች ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ምክክር ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አጎራባች አካባቢዎች መካከል ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ በአጣዬ ከተማ ምክክር ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ እንዲሁም የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ የተገኙ ሲሆን÷ ከሁለቱም ዞን አጎራባች ወረዳዎች የመጡ አመራሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል፡፡

የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ሀላፊ አቶ አረቡ አሊ እንደገለጹት÷ በአካባቢው የሚከሰተውን ግጭት ለማርገብ የሁለቱ ዞን አመራሮች በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው የግጭቱ ተዋናዮች ያቀዱትን ያህል ችግር ሳይፈጥሩ ለማስቆም እንደተቻለም ተናግረዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሀኑ በበኩላቸው÷ ህዝቦችን ለማጋጨት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመገንዘብ የሀገር ሽማግሌዎች እና አመራሮች በቅርበት መስራት መቻላቸው ለቀጣይ በቀጠናው የተረጋጋ እና አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን ያግዛል ብለዋል፡፡

በመድረኩ ግጭቶችን ለማስቀረት የጋራ ስራዎች መሠራት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

በኤልያስ ሹምዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.