Fana: At a Speed of Life!

በጦርነትና በተፈጥሯዊ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመርዳት የተቀናጀ ሀገራዊ የሀብት ማሰባሰብ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነትና በተፈጥሯዊ አደጋዎች ለእርዳታ የተጋለጡ ዜጎችን ለመርዳት የተቀናጀ ሀገራዊ የሀብት ማሰባሰብ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም ከኤልሻዳይ ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር÷ በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሃብት ማሰባሰብ መርሐ ግብርን ይፋ አድርገዋል።
በገቢ ማሰባሰብ መርሐ ግብሩ ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ ዕቅድ መያዙ ተገልጿል።
ድጋፉ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ የወጣት አደረጃጀት መሪነት የሚካሄድ ሲሆን÷ በዚህም ወጣትነት የችግር መንስኤ ነው የሚለውን አመለካከት ለመቀየር ያስችላል ተብሏል።
ድጋፉን ለማሰባሰብ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በቅርቡ አጭር የፅሁፍ መልዕክት መላኪያ ኮድም ይፋ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡
በአጭር የፅሁፍ መልዕክቱ ላይ የሎተሪ እጣዎች እንደሚኖሩ የተጠቀሰ ሲሆን÷ በሁሉም ክልሎች የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚደረግ ታውቋል።
በተጨማሪም በተመረጡ ስፍራዎች የሙዚቃ ድግስ እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው።
የድጋፍ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል።
በአለምሰገድ አሳየ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.