Fana: At a Speed of Life!

በ “ዘ-ጋርዲያን” ለማጭበርበሪያነት የዋለው የዋግኽምራ ተፈናቃይ እናቶች ምስል በፎቶ ጋዜጠኛው ተጋለጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌቲ ኢሜጅስ የፎቶ ጋዜጠኛ ጀማል ኮንተስ ሰቆጣ ላይ ያነሳውን የዋግኽምራ ተፈናቃይ እናቶችን ምስል የእንግሊዙ “ዘጋርዲያን” ጋዜጣ በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መንግስት በፈጸመው በደል የተጎዱ እናቶች በማስመሰል ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በተሳሳተ መረጃ ማጭበርበሩን አጋለጠ፡፡

የጌቲ ኢሜጅስ ጋዜጠኛው ጀማል ኮንተስ ያነሳው ምስል፥ አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ዋግኽምራ ከፈጸመው የሽብር ጥቃት ሸሽተው በሰቆጣ መብራት ኃይል ጣቢያ የተጠለሉትን ተፈናቃይ እናቶች መሆኑን በትዊተር ገጹ አስፍሯል፡፡

ምስሉንም በዚህ ዓመት በፈረንጆቹ መጋቢት 30 ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይፋ እንዳደረገው አመላክቷል።

ነገር ግን ዘጋርዲያን ይህንን ምስል የተጠቀመው “በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ” በተሳሳተ መልኩ ለማሳየት እና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማጭበርበር ነው ሲል የፎቶ ጋዜጠኛው አጋልጧል፡፡

ዘጋርዲያን የፈጸመውን አሳፋሪ ተግባርም አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን ኮንናዋለች፤ እንዲያውም ጀማል ኮንተስ ፎቶውን ሲያነሳ አብራው በሰቆጣ መጠለያ ጣቢያ እንደነበረችም በትዊተር ገጿ ምስክርነቷን ሰጥታለች፡፡

ምስሉ በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉትን እናቶች ሳይሆን የሚያሳየው አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ዋግኽምራ ላይ ከፈጸመው ወረራ ራሳቸውን ለማዳን ሸሽተው በሰቆጣ የሰፈሩትን ተፈናቃይ እናቶች ነው ስትልም ዕውነቱን በትዊተር ገጿ አስፍራለች፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.