Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ9 ወራት ከ 43 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 9 ወራት ከ43 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ሙሉጌታ ተፈራ ÷ ቢሮው በ2014 በጀት ዓመት ከ 48 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ግብር ለመሰብሰብ አቅዶ ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ተናግረዋል።

ቢሮው በግብር አሰባሰብ ሂደት ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ በተሻለ መልኩ መስራቱን ሃላፊው ጠቁመዋል።

በዘጠኝ ወር የተሰበሰበው ግብር ገቢ ለመሰብሰብ ከታቀደው የ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለውም ተመልክቷል፡፡

ቢሮው በዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙ ላይ ወይይት አድርጓል።

በይስማው አደራው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.