ዓለምአቀፋዊ ዜና

ህብረቱ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ ሀይል ለማሰማራት የቀረበውን ሀሳብ እንደሚቀበለው አስታወቀ

By Feven Bishaw

April 26, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ ሀይል ለማሰማራት ያቀረቡትን ሀሳብ በደስታ እንደሚቀበለው አስታወቋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፥ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ለማስተካከል ከቀጠናው የተውጣጣ ወታደራዊ ሀይል በፍጥነት እንዲሰማራ የወሰኑትን ውሳኔ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም መሪዎቹ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል እንዲሁም በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ያለውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እያደረጉ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡