Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን ከኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራ ጋር በትብብር መስራት ትፈልጋለች – የጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን ከኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራ ጋር በተገናኘ በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት የጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ጃይካ) አስታወቀ፡፡
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በፕሮፌሰር ኬኒቺ ኦህኖ ከተመራው የጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ጃይካ) ልዑክ ጋር በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ አተገባበር እንዲሁም ያለበት ደረጃ፣ ውጤት እና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በተጨማሪም የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አተገባበር እና የታለመላቸውን ውጤት ያመጣ ስለመሆኑ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ የሦስት ዓመት ዕቅድ ተግባራዊነት ውጤታማነት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ዶክተር ፍጹም ዕቅዱ ስኬታማ እንዲሆን በዋናነት በአገር በቀል እውቀት እና ክህሎትን ለማጎልበት እንደሚሠራ ጠቁመው፥ ከዚሁ ጎን ለጎን ከውጭ አገራት የሚገኝን ድጋፍ አስፈላጊነት አብራርተዋል፡፡
በተለይ እንደ ጃፓን አይነት አገራት ያለፉበትን ሂደት ማየት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ፍጹም፥ ኢትዮጵያ በቀጣይ ይፋ ከምታደርገው የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ጋር በተገናኘም ምርትን በማሳደግ፣ በሰው ሃብት፣ በተቋም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በተሳካ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራ ላይ ከጃፓን ጋር በትብብር ይሠራል ብለዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው ጃፓን ከኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራ ጋር በተገናኘ በትብብር ለመስራት ያላትን ፍላጎት መግለጻቸውን ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.