መንግስት በኢትዮጵያ የማላዊ አምባሳደር ቻርለስ ፒተር ሞሳ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በኢትዮጵያ የማላዊ አምባሳደር ቻርለስ ፒተር ሞሳ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡
አምባሳደር ቻርለስ ፒተር ሞሳ ÷ ሀገራቸውን በአምባሳደርነት ከማገልገላቸው በተጨማሪ የአፍሪካ ኅብረት እና በአፍሪካ የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ቋሚ ተወካይ በመሆንም ማገልገላቸውን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመላክቷል፡፡
አምባሳደር ቻርለስ ፒተር ሞሳ ሕክምናቸውን በአዲስአበባ ሲከታተሉ ቆይተው ትናንት ሕይወታቸው ማለፉም ተገልጿል፡፡
በአምባሳደር ቻርለስ ፒተር ሞሳ ዕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን መንግስት የገለጸ ሲሆን ለማላዊ መንግስት፣ ህዝብ፣ ቤተሰብ፣ ጓደኞች እና የሥራ ባልደረቦችም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡