Fana: At a Speed of Life!

የጣና ሐይቅ ዳርቻን ለማልማት የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን አስተዳደሩ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣና ሐይቅ ዳርቻን ለማልማት የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
በከተማው ምክር ቤት ዋና እና ምክትል አፈ-ጉባኤ የሚመራ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ዘርፍ፣ የህግና ፍትህ፣ የሴቶችና ህፃናት ቋሚ ኮሚቴ የጣና ዳርቻ መንገዶች ያሉበትን ሁኔታ ጎብኝቷል።
የባህርዳር ከተማ ልማትና ቤቶች ልማት ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ገበያው በላይ የጣና ዳር መንገዶችን ለማልማት ሰፊ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
በተለይም አሮጌው ዴፖ ላይ 4 ነጥብ 27 ሄክታር ቦታ ለማልማት የሚያስችል ፕሮጀክት ተዘጋጅቶ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አሚኮ ዘግቧል።
ዳርቻውን የማልማት ስራውም በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.