Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት” ጥሪን በመቀበል ለሚገቡ እንግዶች በአገልግሎቱ ላይ የ70 በመቶ ቅናሽ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት” ጥሪን በመቀበል ከተለያዩ የዓለም አገራት ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ እንግዶች የ70 በመቶ የሞባይል አገልግሎት ቅናሽ ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ አገልግሎቶቹ እስከ 70 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አሳውቆ÷ ወደ አገራቸው ለመጡ እንግዶችም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
አገልግሎቱን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና በሁሉም የሽያጭ ማዕከሎች ማግኘት እንደሚቻል የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ያመላክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተከትሎ ከተለያዩ የዓለም አገራት እንግዶች ወደ አገር ቤት በመግት ላይ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.