Fana: At a Speed of Life!

ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሐ ግብር በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ያለንን ተካፍለን በጎዳና ላይ እናፍጥር” በሚል መሪ ሀሳብ ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሐ ግብር በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ።

የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት ሀጂ ሙስጠፋ ናስር በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሐ ግብሩ ስለ ሰላምና ስለአንድነት እንዲሁም ያለው ለሌለው መስጠትና መተሳሰብን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

በዛሬው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ከ15 ሺህ በላይ የሚገመቱ ተሳታሪዎች እንደተገኙ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢፍጣር መተጋገዝንና መተሳሰብን ያቀፈ ነው ብለዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩም የሙስሊሞችን የመስጂድ ቦታ ጥያቄ ለመመለስ እንደሚሰራም በዚሂ ጊዜ ተናግረዋዋል፡፡

በተመስገን ቡልቡሎ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.