Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ አንድነትን፣ ፍቅር እና መተሳሰብን ለማጠናከር ያለመ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ተካፍለን፣ ተደጋግፈን እና ተሳስበን እንሻገራለን “በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች፣ የተለዩ የህብረተሰብ ተወካዮች፣ ወጣቶችና የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች የዛሬውን የጋራ ማዕድ የመቋደስ ዝግጅት ያደረግነው የነበረውን የአብሮነት እሴታችንን ለማጽናት በማሰብ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ከክርስትና ዕምነት ተከታዮች ጋር በጋራ ማዕድ የመቋደስ መርሐ ግብር እንደነበር ያስታወሱት ከንቲባ አዳነች፥    ዛሬም ፈጣሪ ረድቶን  በታላቁ የረመዳን ፆም ወቅት በጋራ የአብሮነት ማዕድ ለመቋደስ በቅተናል፤  ይህንን የአብሮነት እሴት  አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አክለውም  ለኢትዮጵያችን ሠላምና  ለአንድነት መጸለይ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፥ የሃይማኖት አባቶችም መቻቻል ፣ አንድነት፣  መተሳሰብና ፍቅር በሕዝቦች መካከል እንዲኖር በርካታ ሥራዎችን ሲሰሩ በመቆየታቸው በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋቸዋል።

ህብረታችን ጥንካሬያችን ፥መተሳሰባችን ጉልበታችን በመሆኑ ሁላችንም ለአገራችን ሠላም ፤ ለልማትና ለአብሮነት አበክረን እንስራ ሲሉም አሳስበዋል።

በትእግስት ስለሺ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.