Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን ሀገራዊ ልዕልናን ባስከበረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ አሻራቸውን ሊያኖሩ ይገባል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሀገራዊ ልዕልናን ባስከበረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ የራሱን አሻራ ሊያኖር እንደሚገባ ምሁራን አመላከቱ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሣይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ጀማል ሰይድ እና ይመር አሊ፥ የውጭ ዲፕሎማሲ የጥንካሬ ምንጭ የሚቀዳው ከሀገር ውስጥ ጠንካራ አንድነት መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም መንግሥት የዜጎችን መከባበር የቀደመባት ለሁሉም የተመቸች እና የተረጋጋች ሀገር ከመፍጠር አኳያ የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል“ ብለዋል፡፡
ለዓመታት የተሻገሩ እዚህም እዚያም ለሚፈጠሩ ግጭቶች መፍትሔ ያመጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ሀገራዊ ምክክሩም ቢሆን ውጤታማ እንዲሆን በቅድሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መግባባት ላይ ሊደርሱ እንደሚገባም ምሁራኑ አመላክተዋል፡፡
የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ለማሻሻል በውስጥ ያለ ሽኩቻን ከመፍታት ባሻገር በውጭ ሀገር ያሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በማደራጀት መጠቀም እንደሚገባም ምሁራኑ ጠቁመዋል፡፡
በሰብለ አክሊሉ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.