Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ – ዩክሬን ጦርነት በፍጆታ ዕቃዎች እና በአገልግሎት ዘርፉ ላይ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ይበልጥ እንዳባባሰው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ዓመት በአውስትራሊያ፣ በአሜሪካ እና በበርካታ የአውሮፓ ሀገራት ሸማቾች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት መከሰቱን ሀገራቱ መጋቢት ወር ላይ ይፋ ባደረጉት የሩብ ዓመት ሪፖርት አመላከቱ፡፡

ሀገራቱ የገንዘብ የመግዛት አቅም ግሽበት እንዳጋጠማቸውም ነው ጉዳዩ በሚመለታቸው የሀገራቱ ስታቲስቲክስ ቢሮዎች በኩል በሪፖርታቸው ይፋ ያደረጉት፡፡

በአውስትራሊያ የሸቀጦች ዋጋ መናር ሸማቾችን ግራ እያጋባ እንደሆነና ከፈረንጆቹ 2000 ወዲህ በፍጆታ ዕቃዎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ይበልጥ እንዳሻቀበም ተነግሯል፡፡

ቢሮው በተለይም በነዳጅ እና በምግብ ፍጆታዎች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መመዝገቡን ነው ዛሬ ይፋ ባደረገው መግለጫው ያመላከተው፡፡

በተመሳሳይ በአሜሪካ በፍጆታ ዕቃዎች እና በአገልግሎት አቅርቦት ላይ የተስተዋለው የዋጋ ጭማሪ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ8 ነጥብ 5 በመቶ አሻቅቧል፡፡

ይህም ከፈረንጆቹ 1981 ወዲህ በአሜሪካ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የተመዘገበበት ዓመት አድርጎታል ተብሏል፡፡

በአሜሪካ ከፍተኛ የዋጋ ማሻቀብ የታየባቸው የፍጆታ ዕቃዎች እና አቅርቦቶች ነዳጅ ፣ መጠለያ እና ምግብ እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የነዳጅ ዋጋ እስከ መጋቢት ወር በ18 ነጥብ 3 በመቶ እንደጨመረና በየዓመቱም የ48 በመቶ የነዳጅ አቅርቦት ዋጋ ጭማሪ እንደሚያሳይ ነው በሪፖርቱ የተመላከተው፡፡

የአሜሪካ የምግብ ዋጋ ንረት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ8 ነጥብ 8 በመቶ መጨመሩን እና ይህም ሸማቾችን ግራ እንዳጋባ ነው የተመለከተው፡፡

በጀርመንም ሸማቾች ላይ የተጫነው የዋጋ ንረት በመጋቢት ወር የሩብ ዓመት ሪፖርት 7 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱ ተጠቁሟል።፡

ሸማቾች ላይ የተጫነው የዋጋ ንረት ጀርመን ከተዋሃደችበት ከፈረንጆቹ 1990 ወዲህ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

አየርላንድ 6 ነጥብ 7 በመቶ ፣ ስፔን 9 ነጥብ 8 በመቶ ፣ እንግሊዝ 6 ነጥብ 2 በመቶ በሸማቾች ላይ የዋጋ መናር መከሰቱን መጋቢት ወር ላይ ባወጡት የሩብ ዓመት ሪፖርታቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

አየርላንድ እንዲህ ያለ የዋጋ ንረት በ40 ዓመት ታሪኳ ውስጥ አይታ እንደማታውቅም ነው ሲ ጂቲ ኤን በዘገባው ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.