Fana: At a Speed of Life!

ጅማ አባ ጅፋር አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ከስራ አገደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ጅማ አባጅፋር አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ከስራ ማገዱ ተገልጿል፡፡
የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ጅማ አባ ጅፋር ያለፉትን አመታት በተለያዩ ጫናዎች ውስጥ ሆኖ ላለመውረድ ሲጫዎት ቆይቷል፡፡
ከነበረበት ጫና ለመውጣት በዘንድሮው የውድድር አመት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በመቅጥር ሊጉን ቢጀምርም በ20 ጨዋታዎች 13 ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
የቡድኑን ውጤት ማጣት ተከትሎ የክለቡ ቦርድ አመራር ከትናንት በስቲያ ግምገማ ያደረገ ሲሆን የቡድኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቀሪ ጨዋታዎች ቡድኑን እንዳይመሩ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ለአሰልጣኙ መታገድ የቡድኑ ውጤት ማጣት እና የአሰልጣኙ እና የተጫዋቾች ግንኙነት መሻከር የክለቡ ቦርድ አመራር ለአሰልጣኙ በፃፈው ደብዳቤ መጠቀሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.