Fana: At a Speed of Life!

የፊቼ ጨምበላላ በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል- የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ እንዳሉት ÷ 1 ሺህ 500 ወጣቶች ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡

የፊቼ ጨምበላላ በዓል ከሲዳማ አልፎ የአለም ቅርስ ሆኗል ያሉት አቶ አለማየሁ በዓሉ ባህልና እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የህብረተሰቡን ደህንነት መጠበቅ ቀዳሚ ስራችን ነው ብለዋል።

ለስራው መሳካት ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተቋም ከሁሉም የፌዴራልና የሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ጋር በጋራ ሰፊ ስራ እየሰሩ መቆየታቸውን ያነሱት አቶ አለማየሁ ተግባሩ እስከ በዓሉ መባቻ ድረስ ይዘልቃል ነው ያሉት።

ለሰላም መጠበቅ የህብረተሰቡ ሚና ግንባር ቀደም ቦታ እንዳለው የቢሮ ሃላፊው ጠቅሰው ማንኛውም አጠራጣሪ ነገር ከተመለከቱ በቶሎ በአቅራቢያቸው ላሉ የጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ ማቅረባቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.