Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተገመገመ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተገመገመ።
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ2014 በጀት አመት የዘጠኝ ወር አፈጻጸም አቅርበዋል።
 
የኑሮ ውድነቱን ለማሻሻል መሰረታዊ ፍጆታ ዕቃዎችን በስፋት የማቅረብ የንግድ ሰንሰለቱን የማሳጠር ስራዎችን በማከናወን በህብረት ስራ ማህበራት በኩል መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች እንዲቀርብ መደረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል።
ለ329 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ከ340 ሺህ 600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉም በሪፖርቱ ተመላክቷል።
 
በተጨማሪ ከመሬት ልማት ጋር ተያይዞ ለ101 የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንደተሰጠ እና ከ74 ሺህ ሄክታር በላይም ለኢንቨስትመንት መሰጠቱን እንዲሁም 383 ሄክታር በህገ ወጥ መንገድ የተወረረ መሬትን ማስመለስ መቻሉን አንስተዋል።
 
በዘጠኝ ወራት ውስጥ 37 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 43 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመድረኩ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ÷ የከተማ አስተዳደሩ የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ላይ አስተያየት በመስጠት በቀጣይም በትኩረት ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.