Fana: At a Speed of Life!

ማዕድ የምግብ ማቀነባበሪያ አክሲዮን ማህበር የሙከራ ምርት ማምረት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ንጋት ኮርፖሬት ማዕድ የምግብ ማቀነባበሪያ አክሲዮን ማህበር ፕሮጀክት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት የሙከራ ምርት ይጀምራል ተባለ፡፡
የአማራ ክልል አፈጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ እንዲሁም የተለያዩ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት የአክሲዮን ማህበሩን ፕሮጀክት ጎብኝተዋል፡፡
በደብረማርቆስ እየተገነባ ያለው የምግብ ማቀነባበሪያው ከአካባቢው አርሶ አደሮች የሚወስደውን ግብዓት ተጠቅሞ የፓስታ ፣ ማካሮኒ ፣ ብስኩትና የስንዴ ዱቄት ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።
የንጋት ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አምላኩ አስረስ ፥ ÷ፕሮጀክቱ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት የሙከራ ምርት የሚጀምርና ከ6 ወር በኋላም መደበኛ ምርት ማምረት እንዲችል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በደብረማርቆስ ከተማ በ86 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈው የማዕድ የምግብ ማቀነባበሪያ አክሲዮን ማህበር ፕሮጀክት በቀድሞው ጥረት በአሁኑ ንጋት ኮርፖሬት ስር ሆኖ ነው በፈረንጆቹ በ2013 መሰረቱ የተቀመጠው።
ይሁንና ለአምስት አመታት የሀብት ማሰባሰብ ስራ ምክንያት ስራው ሳይጀመር ቆይቷል ነው የሚሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው።
ከፈረንጆቹ 2018 ወዲህም ከልማት ባንክ ብድር 75 በመቶው በወቅቱ ባለመለቀቁ የግንባታ ዲዛይን ለውጥ በማጋጠሙና በሌሎች ምክንያቶች ፕሮጀክቱ ሲጓተት መቆየቱን አንስተዋል።
የማዕድ የምግብ ማቀነባበሪያ ወደስራ ሲገባ የስንዴ አምራች ከሆኑት ምስራቅ ጎጃም፣ አዊና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በቀን 250 ቶን ስንዴ ግብዓት ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል ።
በፀጋዬ ወንድወሰን
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.