Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ማሽኖች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በመፈቀዱ የሜካናይዜሽን ግብርናን ሊያዘምኑ የሚችሉ ማሽኖች ቁጥር አድጓል – የግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ማሽኖች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መፈቀዱን ተከትሎ ባለፉት ሁለት አመታት የሜካናይዜሽን ግብርናውን ሊያዘምኑ የሚችሉ ማሽኖች ቁጥር ማደጉን ግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።

ለግብርናው ዘርፍ አገልግሎት ያላቸው ማሽኖች ከረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚያስችል የፖሊሲ ለውጥ ተደርጎ አርሶ አደሩ የግብርና ማሽኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ እድል ተሰጥቷል፡፡

ይህም መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ በሰጠው ትኩረት ሜካናይዜሽኑን በሚፈለገው ልክ ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ እድል መፍጠሩም ተነግሯል።

በዚህም ከሁለት አመታት በፊት በዓመት ወደ ሃገር ውስጥ ይገባ የነበረው 40 እና 50 ትራክተር ሲሆን÷ ባለፉት ሁለት አመታት ግን ከ1 ሺህ 600 በላይ ሆኗል ነው የተባለው፡፡

የግብርና ሜካናይዜሽ ዳይሬክተር አቶ በረከት ፎርሲዶ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ የፖሊሲ ለውጡ በሌላ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶችም ወደ ግብርናው ዘርፍ እንዲገቡ ማበረታቻ ሆኗል ነው ያሉት፡፡

እንዲሁም የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂ በማስመጣት ላይ የተሰማሩ አካላት ቁጥርም ከ50 በመቶ በላይ ማደጉን ተናግረዋል፡፡

በአንድ ዓመት ውስጥ ከ3 እስከ 4 ሺህ ይገባ የነበረው የመስኖ ፓምፕ አሁን ላይ ከ250 ሺህ በላይ የመስኖ ፓምፖች ገብተዋል ነው ያሉት፡፡

ይህም የግብርና ማሽኖች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መፈቀዱን ተከትሎ የመጣ እንደሆነ ነው ያመላከቱት፡፡

በሌላ በኩል የግብርና ማሽን አቅራቢዎችም ማሽኖችን ሲያቀርቡ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት መጠባበቂያ የሚሆን መለዋወጫ እንዲያካትቱና ማሽኖቹ በደረሱበት ሁሉ የጥገና ማዕከላት እንዲኖሩ መመሪያ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡

በይስማው አደራው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.