Fana: At a Speed of Life!

በኢንጂነር አይሻ መሐመድ የተመራ ልዑክ የተንዳሆ መስኖ ልማት ፕሮጀክትን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ የተመራው ልዑክ ከአፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር የተንዳሆ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡
 
ፕሮጀክቱ ሰኔ 2007 ዓ.ም የተጠናቀቀ ሲሆን፥ 60 ሺህ ሄክታር የማልማት አቅም ያለውና ግድቡ 1 ነጥብ 86 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ መያዝ የሚችል መሆኑ ተገልጿል፡
 
ፕሮጀክቱ ከመንግስት በተመደበ 8 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር መገንባቱ ተመላክቷል፡፡
 
ጉብኝቱ የተንዳሆ ግድብና ከግድብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የመስኖ መዋቅሮች የሚያስፈልጋቸውን ጥገና ለመገምገምና 2 ሺህ 500 ሄክታር የማልማት አቅም ያለውና በ433 ሚሊየን ብር በመገንባት ላይ የሚገኘው የተንዳሆ ፒሲ-16 መስኖ ብሎክ ሪሃብሊቴሽንና የጎርፍ መከላከል ዳይክ ጥገና ስራዎች ያለበትን ደረጃ ለመገምገም ያለመ ነው ተብሏል፡፡
 
በጉብኝቱ ላይም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እንድርያስ ጌታ እና ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ እንዲሁም የአፋር ክልል የሚመለከታቸው የቢሮ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.