Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት መንግስታት ለአፍሪካ ቀንድ የድርቅ መቋቋሚያ የሚውል 1 ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጀኔቫ ባካሄደው ጉባኤ ለአፍሪካ ቀንድ ድርቅ መቋቋሚያ የሚውል 1 ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ከለጋሽ አካላት የተሰበሰበው ይህ ገንዘብ በድርቅ ለተጎዱት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅሰብ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

በተለይም በሶማሊያ ስድስት ክልሎች ያለው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ያሰታወቀው ፅህፈት ቤቱ፥ ዝናብ በወቅቱ የማይጥል ከሆነ እና የሰብዓዊ እርዳታ ሄደቱ ካልተጠናከረ በሀገሪቱ አሰከፊ ረሀብ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ለአራት ተከታታይ ጊዜ አነስተኛ የዝናብ መጠን እያገኘ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት አንድ ሚሊዮን የቀጠናው ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን እንዲሁም ሶስት ሚለየን የሚሆኑ የቤት እንስሳት ውሃ እና ግጦሽ በማጣት መሞታቸውን ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ በመግለጫው አመላክቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀውም በሶማሊያ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በምግብ እጦት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በኬንያ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች እንዲሁም በኢትዮጵያ 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች እንዲሁ ለምግብ እጥረት መዳረጋቸውን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.