Fana: At a Speed of Life!

ሴቶች በአይሲቲና በዲጂታል ስራዎች እንዲሰማሩ ለማድረግ በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶች በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅና በዲጂታል ስራዎች እንዲሰማሩና ዲጂታል ኢኮኖሚውን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ በትብብር መስራት እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

ዓለም አቀፍ የልጃገረዶች በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቀን“በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ያሉና ያልተነኩ ዕድሎች ለልጃገረዶች” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን፥ ቀኑ ሴቶችና ልጃገረዶች በዘርፉ ተሳትፏቸው እንዲጨምር፣ ወደ ዘርፉ እንዲሳቡ እና እንዲነቃቁ ለማድረግ ታስቦ የሚከበር መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ አሁን ባለው ዓለም አቀፍ የስራ ስምሪት ከፍተኛ ክፍያ ከሚያስገኙና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ዘርፍ ሴቶችን ያገለለ እንደሆነ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሴቶች በአይሲቲና በዲጂታል ስራዎች እንዲሰማሩና ዲጂታል ኢኮኖሚውን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ በትብብር መስራት ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በሴቶች ላይ የሚጋረጡ ልዩ ልዩ ማህበራዊ መሰናክሎችን መፍታት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በዓለማችን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ልጃገዶች 18 በመቶ ብቻ ሲሆኑ የወንዶቹ ድርሻ ደግሞ 35 በመቶ ነው ተብሏል።

በክላውድ ኮምፒዩቲንግ 14 በመቶ፣ በምህንድስና 20 በመቶ፣ በዳታና የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሴቶቹ ድርሻ 32 በመቶ ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.