የሀገር ውስጥ ዜና

ሴቶች በአይሲቲና በዲጂታል ስራዎች እንዲሰማሩ ለማድረግ በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

By Feven Bishaw

April 27, 2022

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶች በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅና በዲጂታል ስራዎች እንዲሰማሩና ዲጂታል ኢኮኖሚውን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ በትብብር መስራት እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

ዓለም አቀፍ የልጃገረዶች በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቀን“በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ያሉና ያልተነኩ ዕድሎች ለልጃገረዶች” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን፥ ቀኑ ሴቶችና ልጃገረዶች በዘርፉ ተሳትፏቸው እንዲጨምር፣ ወደ ዘርፉ እንዲሳቡ እና እንዲነቃቁ ለማድረግ ታስቦ የሚከበር መሆኑ ተገልጿል፡፡