በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ የሚከናወነው የጓሮ ግብርና ተጎበኘ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት ጋር የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የስብሰባው ተሳታፊዎች የከተማ ግብርና እንቅስቃሴ አንድ አካል የሆነውን እና በጽሕፈት ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚከናወነውን የጓሮ ግብርና ገምግመዋል።
የጓሮ ግብርና የሚካሄድባቸው ስፍራዎች የእንስሳት መኖ እንዲሁም ማዳበሪያ ለናሙና የሚመረትባቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
ውሃን ያለብክነት መጠቀም መቻልን፣ ቁሳቁሶችን እንደገና በጥቅም ላይ ማዋልን እና የቦታ እጥረትን ባማከለ ሁኔታ ግብርናን መከወን እንደሚቻል በማሳየት የከተማ ነዋሪዎች የከተማ ግብርናን እንዲተገብሩ ሊበረታቱ ይገባል መባሉም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!