የሀገር ውስጥ ዜና

በሐዋሳ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

By Feven Bishaw

April 27, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሐዋሳ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን መረቁ፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ ÷ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ ፣የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የሐዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ አሩሳ ተገኝተዋል።