Fana: At a Speed of Life!

ከሳዑዲ ዓረቢያ 1ሺህ 28 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 28 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
 
ከተመላሾቹ ውስጥ አራቱ ህጻናት ሲሆኑ÷1ሺህ 24 የሚሆኑን ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡
 
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተመላክቷል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.