Fana: At a Speed of Life!

ካናዳ በአፍሪካ ቀንድ በምግብ እጥረት ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመርዳት የ73 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የካናዳ መንግስት በአፍሪካ ቀንድ በምግብ እጥረት እና በሌሎች ምክንያቶች ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የሚሆን 73 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

ድጋፉ ኢትዮጵያን፣ ኬንያ እና ሶማሊያን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ መገለፁን በኢትዮጵያ የካናዳ ኤምባሲ አስታውቋል።

የገንዘብ ድጋፉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ፣ በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ንቅናቄ እና በመንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በኩል ፈጣን እና የረዥም ጊዜ ፍላጎቶችን ለማሟላት ይሰጣል ነው የተባለው::

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.