የሀገር ውስጥ ዜና

በባሕርዳር ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ዝግጅት ተካሄደ

By Alemayehu Geremew

April 27, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕርዳር ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ዝግጅት ተካሄደ።

የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅት የባሕር ዳር ከተማና በአካባቢው የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ነው የተካሄደው።

በዝግጅቱ ላይ የክርስትና እና የሌሎች ሃይማኖቶች ተከታይ አባቶች መገኘታቸውን የአሚኮ ዘገባ ያመላክታል።

የሃይማኖት አባቶች በዝግጅቱ ላይ የመከባበርና የአብሮነት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።