የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ራስል ጋር ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

April 27, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አዲስ ከተሾሙት የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ራስል ጋር ተወያይተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ በኢትዮጵያ በሰው ሠራሽና በተፈሮ አደጋ የተጎዱ በርካታ ሕጻናትን ሁኔታ በቦታው ተገኝቶ ለማየትና ለመርዳት የሚያስችላቸውን የዓለም አቀፍ ከፍተኛ ድጋፍ ለማስገኘት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የመስክ ሥራ ልምድ ያለው ሲሆን ግንኙነቱን በማሻሻልና በማጠናከር መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል።