Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል ሀዋሳ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ “ፍቼ ጫምባላላ” ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ሀዋሳ ገብተዋል።
ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ በተጨማሪ አምባሳር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የክልልና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና እንግዶችም በበዓሉ ላይ ለመታደም ሀዋሳ ገብተዋል።
በሀዋሳ ዶሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.