በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስታት መካከል የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ተፈርሟል፡፡
እርዳታው የምግብ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ በምግብ ገበያና በምግብ ዝግጅት ወቅት የሚከሰተውን የምግብ ጥራትና ንጽህና መጓደልን በመከላከል የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ ለታቀደው ፕሮጀክት የሚውል መሆኑ ታውቋል፡፡