በሐረሪ ክልል የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ነው – የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አስወቀ፡፡
የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ÷ በክልሉ በየዘርፉ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለዚህም እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው÷ በቀጣይም እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ሕዝቡ ለሚያነሳቸውን ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ እንዲያገኝም አመራሩ በላቀ ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት መንቀሳቀስ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
ዛሬ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በየዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር ባካሄደው የግምገማ መድረክ÷ በተለያዩ ተቋማት የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት ማብራሪያና ሪፖርት ቀርቧል።
በቀረቡት ሪፖርተሮች እንደተመላከተውም የማህበረሰቡን የኑሮ ችግር ከማቃለልና ገበያውን ከማረጋጋት አንጻር የምግብ ነክ አቅርቦቶችን የማሳደግ እና ከባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የመደገፍ ስራ መሰራቱ ተገልጿል፡፡
የክልሉን ሰላምና ደህንነት ከማረጋገጥ አኳያ፣ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራንና ሕገ ወጥ የቤት ግንባታዎችን በመቆጣጠር ረገድ፣ ከታክሲ አገልግሎት ታሪፍና ከስምሪት ጋር በተያያዘ ታርጋ ሳይለጥፉ በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ አኳያ አበረታች ሥራ መሰራቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡