Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በመጪው ክረምት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የቡና ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው – የክልሉ ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በመጪው ክረምት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የቡና ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መሃመድ ሳኒ አሚን በክረምት ለሚደረገው የቡና ተከላ መርሃ ግብር የተሻለ ጥራት ያላቸው የቡና ዝርያዎች እየተዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ለቡና ጥራት ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን የገለጹት ሃላፊው፥ በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

በመጪው ክረምት በክልል ደራጃ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የቡና ችግኝ ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ከዚህ ውስጥም 300 ሚሊየን የሚሆነውን የቡና ችግኝ በጅማ ዞን ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ መናገራቸውን ከክልሉ ግብርና ቢሮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.