Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ለቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በ470 ሚሊየን ብር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በዘንድሮው ዓመት በ470 ሚሊየን ብር ወጪ የተለያዩ ተግባራትን እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ÷ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ በክልሉ መኖሩ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል በኩል እያመጡ ያሉት ተጨባጭ ለውጦች ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም አመላክተዋል።
በጋምቤላ ክልል የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር ቢየል ቢቾክ ፕሮጀክቱ÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዲማ ፣ መንገሺ ፣ ጆር፣ ኢታንግ፣ ላሬ፣ ጅካዎ ፣ ማኩዋይ እና ዋንቱዋ ወረዳዎች ላይ በርካታ ተግባራት አከናውኗል ብለዋል፡፡
በአርብቶና በከፊል አርሶ አደሩ አካባቢዎች የተቀናጀ ልማት ማፋጠን፣ የእንስሳት እርባታን ማሻሻልና ገበያ ማስፋፋት፣ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶችን ማዘመንና የሰው ኃይልን ማብቃት የፕሮጀክቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች መሆናቸውንም አስረድተዋል።
በክልሉ በስምንቱ ወረዳዎች ለተነደፉት ስራዎች የጤና፣ ትምህርት፣ መንገድ፣ ግብርናና ሌሎችም የልማት ዘርፎች ማስፈፀሚያ 470 ሚሊየን ብር ተመድቧል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.