Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለሃብቶች በክልሉ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በማዕድን፣ ቅመማ ቅመምና እንስሳት ሃብት ላይ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ክልሉ በዚሁ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታዎች ማመቻቸቱንም ነው የገለጸው።
የክልሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኋላፊ አቶ ተመስገን ከበደ በከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብት በበለጸገው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መዋዕለ ነዋይን ማፍሰስ አዋጭ መሆኑን ገልጸዋል።
በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚታዩ የአሰራር ውጣ ውረዶችን በመቅረፍ በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶች በስራቸው ውጤታማ የሚሆኑበት ስርአት መዘርጋቱንም ተናግረዋል።
የመሬት አቅርቦት ፣ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል መኖሩም የዘርፉን ስኬታማነት እንሚያጎላው አመልክተዋል።
ባለሃብቶቹ በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ በሚመረቱትና በገበያ ተፈላጊ በሆኑት የቅመማ ቅመም፣ የማርና የቡና ምርቶች ላይ ሀብታቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል በእንስሳት ሃብት ልማት፣ ወርቅና ብረት ማዕድኖች ባለሃብቶች የሚያለሙበት አማራጭ እንዳለ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.