Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል በ2014 አረንጓዴ አሻራ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል መዘጋጀቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል በ2014 የክረምት ወራት በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቋል።
የሐረር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ምስራ አብደላ እስከ አሁን ባለው የዝግጅት ሂደት 2 ሚሊየን ችግኞች መዘጋጀታቸውን ገልጸው÷ ለአርሶ አደሮችና ለግብርና ልማት ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ለመተከል በዕቅድ ከተያዘው 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኝ ውስጥ 960 ሺህ ያህሉ የደን እንዲሁም 2 ነጥብ 4 ሚሊየኑ ደግሞ ለምግብ ዋስትና የሚውሉ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡
በሐረሪ ክልል ባለፉት ሦስት ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 11 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ መረጃ ያመላክታል ።
በምንያህል መለሰ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.