Fana: At a Speed of Life!

ሙዋይ ኪባኪ ለኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ነበሩ-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ሙዋይ ኪባኪ አስከሬን ሽኝት መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል፡፡
 
በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ሙዋይ ኪባኪ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅነታቸውን በተግባር ያረጋገጡ መሪ ነበሩ ብለዋል፡፡
 
ለአብነትም ኪባኪ በስልጣን ዘመናቸው ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለቀጠናው ልማት ወሳኝ የሆኑ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም በኢጋድ ማዕቀፍ ስር በመሆን በሶማሊያ እና ሱዳን የተደረጉ የሰላም ጥረቶችን በቁርጠኝነት ሲደግፉ እንደነበር አውስተዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለኬንያ ህዝብ እንዲሁም ለኪባኪ ወዳጅ ዘመዶች እና ቤተሰቦች መጽናትን ተመኝተዋል፡፡
 
ሙዋይ ኪባኪ በስልጣን ዘመናቸው ኬንያን በተለያዩ ዘርፎች በተለይም በኢኮኖሚው የተሻለ እምርታ እንድታስዝመዘግብ የበኩላቸውን ሚና መጫወታቸው ይነገራል፡፡
 
የኬንያ 3ኛው ፕሬዚዳንት የነበሩት ሙዋይ ኪባኪ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ነው ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.