Fana: At a Speed of Life!

ጥፋትን በጥፋት ነውርን በነውር አናክመውም- ኡዝታዝ አቡበከር አህመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከኢድ እስከ ኢድ መርሃ ግር አካል የሆነው ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
 
ኡዝታዝ አቡበከር አህመድ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ሰሞኑን በአንዳንድ አካባቢዎች መሆን የማይገባቸው እና ኢትዮጵያውያንን የማይገልጹ ጸያፍ ድርጊቶች መፈጸማቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ነውረኛ ተግባር የሚፈጽሙ ሁሉ ተገቢው ህጋዊ ቅጣት ማግኘት አለባቸው ያሉት ኡዝታዝ አቡበከር÷ይሁን እንጂ ጥፋትን በጥፋት ነውርን በነውር አናክመውም ነው ያሉት፡፡
 
ቀሳውስት አባቶች የእስልምና ዕምነት አባቶች ይህን በአገራችን የተከሰተውን ጥፋት አውግዘዋል፤ይህ አንድነታችን ነው የሚያምርብን፤ጥያቄያችንንም በሰላማዊ መንገድ በማቅረብ ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ አለብን ብለዋል።
 
የጋራ አንድነት በሚንጸባረቅብት መንገድ ኢፍጣሩ እንዲዘጋጅ ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.