በፕሪሚየር ሊጉ ጅማ አባ ጅፋር ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ ድል አስመዝግቧል
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ21ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር ከባህር ዳር ከተማ ተገናኝተዋል።
ጨዋታውን ጅባ አባ ጅፋር 2 ለ 0 ሲያሸንፍ አስጨናቂ ፀጋዬ እና ሱራፌል አወል የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ጅማ አባ ጅፋር ያስመዘገበው ውጤት ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ የተገኘ ድል ነው።
ማምሻውን በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ መከላከያ ኢትዮጵያ ቡናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል።
ጨዋታው በመከላከያ 4 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ተሾመ በላቸው፣ ቢንያም በላይ፣ አዲሱ አቱላ እና አሚን ነስሩ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ተጨማሪ መረጃ ከሶከር ኢትዮጵያ