በአዲስ አበባ የተዘጋጀው የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሐ ግብር በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት ግብረ ኃይል አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተዘጋጀው የጎዳና ላይ ታላቅ የኢፍጣር መርሓ ግብር ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
ለመርሓ ግብሩ በሠላም መጠናቀቅ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች እና ሁልጊዜም የተሰጠውን ሠላምና ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት በሙሉ ቁርጠኝነት ለሚወጣው የፀጥታ ኃይል እንዲሁም ለህዝበ ሙስሊሙ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
መላው የከተማዋ ነዋሪዎች በመቻቻልና በመከባበር ጠብቆ ያቆያቸውን መልካም እሴቶችም አጠናክሮ በመቀጠል ለከተማዋ ሠላም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክትም የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥሪ ማቅረቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።