Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መጪውን የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በወልድያ የሚገኙትን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዕዞች ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መጪውን የኢድ አልፈጥር በአል ምክንያት በማድረግ በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ የሚገኙትን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የደቡብ፣ ምሥራቅ፣ 6ኛ እና 8ኛ ዕዞችን ጎብኝተዋል።
 
በወልድያ ከተማ በተዘጋጀው የጉብኝት ስነ ስርዓት ከሰራዊቱ አባላት ባለፈ የከተማዋ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሰራዊቱ አባላት በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
ኢትዮጵያ ለሺህ ዘመናት ክርስትናና እስልምና በፍቅር የኖሩባት ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ይህ የኩራታችን ምንጭ ነው ብለዋል።
 
ኢትዮጵያ የሚነገር ታሪክ ብቻ ሳይሆን የሚለማ መሬት እና የሚያለማ ህዝብ አላትም ነው ያሉት።
 
ይህንን የተረዱ ጠላቶቻችን ልማታችንን ለማደናቀፍ እና አንድነታችንን ለማጠልሸት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
 
ኢትዮጵያን በጥላቻ ታውሮ ማሸነፍ እንደማይቻል ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በፍቅር ተነሳስቶ መስዋዕትነት ከፍሎ ኢትዮጵያን ማጽናት ነው የሚቻለው ብለዋል።
 
ፈታናዎች እና የሚያደናቅፉን ቢበዙም በየቀኑ እየበረታን እንሄዳለንም ነው ያሉት።
 
የኢትዮጵያ የመጀመሪያውም ሆነ የመጨረሻው ምሰሶ የሀገር መከላከያ እንደሆነም አስታውቀዋል።
 
በአልአዛር ታደለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.