የሀገር ውስጥ ዜና

የሴቶች የኢኮኖሚ ብቃት ፎረም በብሔራዊ ደረጃ ተቋቋመ

By Feven Bishaw

April 30, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የሴቶችን የኢኮኖሚ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተቀናጀ መልኩ ለመስራት የሚያስችል የሴቶች የኢኮኖሚ ብቃት ፎረም ዛሬ በብሔራዊ ደረጃ ተቋቁሟል፡፡

በፎረሙ መመስረቻ መርሃ ግብር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኦሞድ ÷ፎረሙ ሴቶች በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ መሰናክል የሆኑባቸውን ችግሮች በጥናት በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ፣ የሴቶችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከርና በሴቶች መካከል የሚደረገው የልምድ ልውውጥ የሀብት ብክነትንና የስራ ድግግሞሽ ለማስቀረት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡