Fana: At a Speed of Life!

ከ92 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ92 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባለፈው ሳምንት ባደረገው ክትትል 90 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፎች መያዛቸው አሳውቋል፡፡

 

ሞያሌ 25 ነጥብ 2 ሚሊየን፣ ድሬድዋ 19 ነጥብ 7 ሚሊየን እና ጅግጅጋ 11 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ እንደቻሉ ተጠቅሷል፡፡

 

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያንቀሳቅሱ የተገኙ 10 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

 

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎችም÷ አልባሳት፣ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ተሽከርካሪዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.