የሀገር ውስጥ ዜና

በድሬዳዋ ከተማ በነበረው ሁከት ተሳታፊ የነበሩ 89 ተጠርጣሪዎች ተያዙ

By Feven Bishaw

April 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትላንትናው እለት በድሬዳዋ ከተማ በነበረው ሁከት ተሳታፊ የነበሩ 89 ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለጸ፡፡

በእለቱ የነበረውን ሁከት አስመልክቶ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ እና የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምርያ የህዝብ ግንኙነትና የለውጥ ስራዎች ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ በጋራ በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡