የሀገር ውስጥ ዜና

1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ከነገ በስቲያ ሰኞ ይከበራል

By Feven Bishaw

April 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ከነገ በስቲያ ሰኞ ሚያዝያ 24 ይከበራል ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደገለፀው ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን ባለመታየቷ በዓሉ ከነገ በስቲያ ሰኞ ይከበራል።