Fana: At a Speed of Life!

በድርቅ ለተጎዱ የሶማሌ ክልል ወገኖች ከ27 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድርቅ ለተጎዱ የሶማሌ ክልል ወገኖች የሚሆን ከ27 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ ተደረገ፡፡

ድጋፉ ሜንስቸን ፉር በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት የተበረከተ ሲሆን÷ በ25 ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ጅግጅጋ እንደደረሰ ተገልጿል፡፡

ድጋፉን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተረክበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ግብረሰናይ ድርጅቱ በድርቅ ለተጎዱ የሶማሌ ክልል ወገኖች ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ እርዳታው በድርቅ ለተጎዱ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ይከፋፈላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎችን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይልማ ታዬ በበኩላቸው÷ ድርጅታቸው በሶማሌ ክልል በመሰረተ ልማት አገልግሎቶች በውሃ፣ በትምህርት፣ በጤና እና የህብረተሰቡን ህይወት በሚለውጡ ፕሮጀክቶች ላይ ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.